EIADE Services

የምንሰጣቸው አገልግሎቶች

ኢሙዳት የሙስሊሙን ማህበረሰብ ለመደገፍ እና ኢስላማዊ እሴቶችን በትምህርት፣ በበጎ አድራጎት እና በማህበረሰብ ልማት ለማስተዋወቅ የተለያዩ አገልግሎቶችን ይሰጣል።

ለማህበረሳብችን የምንሰጣቸው አገልግሎቶች

ኢሙዳት የሙስሊሙን ማህበረሰብ መንፈሳዊ እና ቁሳዊ ፍላጎቶችን ለማሟላት የተለያዩ መርሃ ግብሮች እና ውጥኖች በመንደግ በማገልገል ላይ ይገኛል።

ለአናሳ ማህበረሰቦች ኢስላማዊ ትምህርት

ሙስሊሞች ጥቂት በሆኑባቸው አካባቢዎች ላሉ ሙስሊሞች የተዋቀረ ኢስላማዊ እውቀትን ለማዳረስ የተለያዩ ኮርሶችን እና የትምህርት ፕሮግራሞችን ማዘጋጀት እና መስጠት

የመስጂድ እና መድረሳዎች ግንባታና ድጋፍ

የአምልኮ፣ የመማሪያ እና የማህበረሰብ ድጋፍ ማእከል ሆነው እንዲያገለግሉ በማሰብ የመስጊዶችን እና መድረሳዎችን ግንባታ እና እድሳት መርዳት

ተጋላጭ ለሆኑ ሙስሊሞች የገንዘብ ድጋፍ

በድህነት ምክንያት ለሚሲዮናዊ ጫና ተጋላጭ ለሆኑ ሙስሊሞች የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ ክብራቸው እና እምነታቸው መጠበቁን ማረጋገጥ

የንፅፅር ትምህርት እና የዳዕዋ እንቅስቃሴዎች

ሙስሊሞች ስለተለያዩ እምነት እውቀት እንዲኖራቸው እና ውጤታማ የዳዕዋ እንቅስቃሴ ላይ ይሳተፉ ዘንድ የተለያዩ ኮርሶችን መስጠት

ለሁለተኛ ደረጃ እና ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እና ወጣቶች አቅም ግንባታ

በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እና ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ያሉ ሙስሊም ተማሪዎች እና ወጣቶች ኢስላማዊ ማንነታቸውን እና ጽናታቸውን እንዲያጠናክሩ እና በዕውቀት የሚመሩ፣ ንቁ የማህበረሰብ መሪዎች እንዲሆኑ የሚያግዙ ፕሮግራሞችን ማዘጋጀት

የማህበረሰብ ተደራሽነት እና ዳዕዋ

እስልምናን በጥበብ እና ግልጽ በሆነ መንገድ ለማስፋፋት የዳዕዋ ዘመቻዎችን፣ ህዝባዊ መድረኮችን እና ውይይቶችን በማዘጋጀት

ኢስላማዊ ሥነ-ጽሑፍ እና የሚዲያ ስርጭት

በሃገር ውስጥ ቋንቋዎች ትክክለኛ ኢስላማዊ መጽሃፎችን፣ ፓምፍሌቶችን እና የመልቲሚዲያ ቁሳቁሶችን ማምረት እና ማከፋፈል

ዳኢዎችን ማሰልጠን

ዳኢዎች ማህበረሰባቸው በብቃት ለማገልገል፣ ለመምራት እና ለማስተማር የሚያስፈልጓቸውን ልምዶች ያዳብሩ ዘንድ ስልጠናዎችን ማዘጋጀት

የምንሰጣቸው አገልግሎቶች ፕሮግራሞች

የማህበረሰባችንን የተለያዩ ፍላጎቶች ለማሟላት ስለተቀረጹ አጠቃላይ የአገልግሎት ፕሮግራሞቻችን የበለጠ ይወቁ።

ማህበራዊ አገልግሎቶች

ማህበራዊ አገልግሎቶች

የኢኮኖሚ ችግር ያለባቸው ሙስሊም ቤተሰቦችን በምግብ ማከፋፈል፣ የገንዘብ ድጋፍ እና አስፈላጊ አቅርቦቶችን ጨምሮ በታለሙ የእርዳታ ፕሮግራሞች እንረዳለን።

ዋና ዋና ተግባራት:

  • የአደጋ ጊዜ የገንዘብ ድጋፍ እና ማህበራዊ እርዳታ
  • ከ12,000 በላይ የምግብ ፓኬጆች ተሰራጭተዋል
  • ለመበለቶች እና ወላጅ አልባ ህጻናት የሚደረግ የተለየ ድጋፍ
  • የጤና አገልግሎት እና በረመዳን የገጠር የኢፍጣር መርሃ ግብሮች
  • የገጠር የሚኖሩ ታዳጊዎች ኢስላማዊ ትምህርት ላይ እንዲያተኩሩ የሚረዳ የፍየል ፕሮጀክት

12,000+

የምግብ ፓኬጆች

3,500+

የተረዱ ቤተሰቦች

250+

በጎ ፈቃደኞች

በተደጋጋሚ የሚጠየቁ ጥያቄዎች

ስለ አገልግሎቶቻችን እና እንዴት እነሱን ማግኘት እንደሚችሉ ላለዎት ጥያቄዎች መልሶችን ያግኙ።

አገልግሎታችን ለሁሉም የማህበረሰቡ አባላት ከፍት ናቸው። ስለፕሮግራሞቻችን እና እንዴት ማግኘት እንደሚችሉ የበለጠ ለማወቅ ቢሮአችንን መጎብኘት፣ በድረ-ገፃችን ወይም በስልክ ሊያነጋግሩን ወይም በምናዘጋጃቸው ፕሮግራሞች ላይ በመገኘት መጠየቅ ይችላሉ።
የገንዘብ ልገሳዎችን፣ ጊዜዎን እና ችሎታዎን በበጎ ፈቃደኝነት ወይም በልዩ ፕሮጄክቶች ላይ ከእኛ ጋር መተባበርን ጨምሮ ኢሙዳትን ለመርዳት ብዙ መንገዶች አሉ። የበለጠ ለማወቅ የመዋጮ ገጻችንን ይጎብኙ ወይም ያግኙን።
አዎ፣ አገልግሎቶቻችንን በመላው ኢትዮጵያ ወደ በርካታ ክልሎች አስፋፍተናል። የጤና አገልግሎታችን፣ የውሃ ፕሮጀክቶቻችን እና የትምህርት ፕሮግራሞቻችን በመላው አገሪቱ በገጠር እና ራቅ ባሉ አካባቢዎች ላሉ ማህበረሰቦች እየደረሱ ይገኛሉ።
የአገልግሎት ጥያቄዎን በድረ-ገፃችን በኩል ወይም በቀጥታ ቢሮአችንን በመገኘት ማቅረብ ይችላሉ። ቡድናችን የማህበረሰቡን ፍላጎቶች ካሉን ሀብቶች እና የፕሮግራም አካባቢዎች ጋር በመገምገም እንዴት በተሻለ ሁኔታ መርዳት እንደምንችል ይወስናል።

ጥያቀዎ እዚህ ውስጥ የለም? ለበለጠ መረጃ እና ለማንኛውም ጥያቄ ያግኙን።

ለመሳተፍ ዝግጁ ነዎት?

አገልግሎቶቻችንን ለማግኘት፣ በጎ ፍቃደኛ ለመሆን ወይም ስራችንን ለመደገፍና ማህበረሰቡን ለማገልገል የሚፈልጉ ወንድምና እህቶችን ተሳትፎዎን በደስታ እንቀበላለን።

አገልግሎት ይጠይቁ

እርዳታ ይፈልጋሉ? አገልግሎቶቻችንን ለቤተሰብዎ ወይም ለማህበረሰብዎ ይጠይቁ።

ለመጠየቅ

በጎ ፈቃደኛ ይሁኑ

በማህበረሰቡ ውስጥ ለውጥ ለማምጣት ጊዜዎን እና ችሎታዎን ያካፍሉን።

በጎ ፈቃደኛ ለመሆን

ስራችንን ይደግፉ

አገልግሎታችንን እንድንቀጥል ለመርዳት እና የበለጠ ለማስፋት ይረዳን ዘንድ ይለግሱ።

ለመለገስ